ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
157

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በሀገር ውስጥ ገበያ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ካለቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች አውቶሞቢል፣ 30 ሰው የሚጭን መለስተኛ ተሸከርካሪ እና 60 ሰው የሚጭን ከፍተኛ ተሽከርካሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ ኬሚካልና ተዛማጅ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፣ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት  ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መሥሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መሥሪያ ቤት /ባሕር ዳር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. የተሽከርካሪ ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያ መሰረት በተገለጸው የሥራ ቀናት በታሸገ ኢንቮሎፕ ፖስታ የቴክኒካል ማወዳደሪያ ሰነድ፤ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ሲፒኦ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የድርጅታሁን ማህተም በማድረግ ኢንተርፕራይዙ ለዚሁ ጉዳይ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
  7. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች ባሕር ዳር በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ ዋና መሥሪያ ቤት መጋዝን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀው ውስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ ሃምሳ በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15/ 09 18 01 69 35 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here