በአፈ/ከሣሽ መ/ታ ፍሬው አስረስ ጠበቃ ደምለው ሞገስ እና በአፈ/ተከሣሽ እነ መላኩ ተክሌ 2ቱ ራሣቸው መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈፃፀም ተከሣሽ እንደ ፍርዱ ያልፈፀሙ በመሆኑ በሁለተኛ አፈ/ተከሣሽ በአቶ ጌትነት መንግሥት ስም በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 02 በምሥራቅ ቦሰና ወሌ፣ በምእራብ መንገድ፣ በሰሜን ወንድምአገኝ የኔው እና በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው 200 ካሬ ሜትር ያረፈ መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 2,489,111/ሁለት ሚሊየን አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሸህ አንድ መቶ አስራ አንድ/ ብር ሆኖ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ ፤መጫረት የምትፈልጉ ቤቱ በሚገኝበት እንጅባራ ከተማ ቀበሌ 02 ቀርባችሁ እንድትጫረቱ፡፡ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ¼ኛውን የሚያሲዝ ሲሆን የጨረታ ቀኑ ሐምሌ 30/2016 ውጤቱ የሚገለጽ መሆኑን እንዲያውቁት ፍ/ቤቱ አዟል፡፡