በአንድ ድንጋይ

0
132

በትልልቅ ከተሞች መኖሪያ ቤት እና ከባቢ ዓየሩን ለማቀዝቀዝ ዕፅዋትን ከመትከል እና ከፀሀይ ኃይል መሰብሰቢያ ንጣፍ በሚገኝ ኃይል ለማቀዝቀዝ ከመገልገል ጣሪያን ነጭቀለም መቀባት ወይም በአንፀባራቂ መሸፈን የበለጠ ውጤታማ መሆኑን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

በእንግሊዝ የለንደን ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት ጣሪያን ነጭ ቀለም መቀባት ወይም በአንፀባራቂ መሸፈን ከፀሀይ ንጣፍ በሚገኝ ኃይል ተገልግሎ ከማቀዝቀዝ እና ዕፅዋትን ከመትከል የበለጠ ውጤታማ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በኤሌክትሪክ ኃይል ዓየሩን ለማቀዝቀዝ መሞከርም ለንደንን በመሳሰሉ በትልልቅ ከተሞች እስከ አንድ ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሙቀቱ እንዲጨምር ያደርጋል ነው ያሉት – ተመራማሪዎቹ፡፡

ተመራማሪዎቹ በለንደን ከተማ ባደረጉት አሰሳ እና በወሰዱት ልኬትም ጣሪያን በነጭ ቀለም መቀባት ወይም  በአንፀባራቂ መሸፈን በአማካይ አንድ ነጥብ ሁለት ዲግሪ  ሴንቲግሬድ የሙቀት መጠንን ይቀንሳል፡፡

በተመሳሳይ ከህንፃ ውስጥ ሙቀትን ወደ ውጪ ማስወጣት የከተማውን ከባቢ ዓየር ዜሮ ነጥብ 15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደ ማዕከላዊ የለንደን ከተማ አካባቢዎችን ደግሞ አንድ ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ያህል ሙቀቱ እንዲጨምሩ ያደርጋል ነው ያሉት – ተመራማሪዎቹ፡፡

በለንደን ከተማ መኖሪያ ቤትንም ሆነ ከባቢ ዓየሩን ለማቀዝቀዝ በ2018 እ.አ.አ ተከታታይ ሙከራዎች መካሄዳቸውን የገለጹት የጥናትና ምርምሩ መሪ ጣሪያን በነጭ ቀለም መቀባት ወይም አፀባራቂ ማልበስ ከአንድ ነጥብ ሁለት እስከ ሁለት ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሙቀት መጠንን እንደሚቀንስ ነው ዕማኝነታቸውን የሰጡት፡፡

ተመራማሪዎቹ ጣሪያን ነጭ ቀለም ወይም አንፀባራቂ ከማልበስ ባሻገር ያሉት የተሞከሩት ስልቶች የተለያዩ የጐንዮሽ ጠቀሜታ ቢኖራቸውም ውጤታማነታቸው ከተመረጠው ስልት የተሻለ አለመሆኑን ነው የተገነዘቡት:: በመጨረሻም ሙቀትን አንፀባርቆ መመለስ አስርጐ ከማስገባት የበለጠ “በአንድ ድንጋይ…” እንዲሉ ከባቢ ዓየርንም መኖሪያ ቤቶችንም እንደሚያቀዘቅዝ ነው ያደማደሙት፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here