በገፅቅብ – ምስል ሲያብብ

0
155

ቻይናዊቷ ወጣት የተለያዩ መስመሮችን እና የገፅ ቅብ  መኳኳያ ቀለማትን በመጠቀም የ66 ዓመት አያቷን ምስል ሰላሳ ዓመታት ወደ ኃላ መልሳ ወጣት የተንቀሳቃሽ ምስል ገፀ ባህሪ መስራቷን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል፡፡

በማህበራዊ ድረ ገፆች “sakuralusi’’ በሚል መለያ የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የምታጋራው ወጣት የገፅ ቅብ ባለሙያ የአያቷን ምስል በገፅ ቅብ የ30 ዓመት ወጣት አስመስላ የለቀቀቻቸው ምስሎች ከቻይና አልፎ በቬትናም እና በምዕራባውያን ሃገራትም ዝናን አትርፎላታል፡፡

ወጣቷ ቀደም ብሎ በቻይና ዶይን በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ በቲክ ቶክ ምስሎችን ታጋራ እንደነበር ነው የተገለፀው፡፡ ወጣቷ የአያቷን ምስል በገፅ ቅብ ችሎታዋ ወጣት አስመስላ ሰርታ የለቀቀችው ምስል ከሁሉም በላይ የተለየ አድናቆት እና እይታ አስገኝቶላታል፡፡

የገፅ ቅብ ባለሙያዋ የምትሰራቸው የተንቀሳቃሽ ምስል ወካዮች የተለዩ፣ ሳቢና አስደናቂ በመሆናቸውም በቀጣይ የተመልካቾቿ ቁጥር በብዙ ዕጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

በቅርቡ የለቀቀችው የአያቷ በገፅ ቅብ ወደ ወጣትነት የተቀየረው ምስልም ወደፊት በዚሁ መስክ የተመልካችን ቀልብ የሚገዙ በርካታ ውጤቶችን ልታበረክት እንደምትችል  ባለ ተስፋነቷን አመላካች መሆኑ ተሰምሮበታል – በድረ ገጹ ጽሁፍ፡፡

“ሳኩራሊስ” በሚል ከምትታወቀው የገጽ ቅብ ባለሙያ ባሻገር በቻይና በርካታ ወጣት የገጽ ቅብ ባለሙያዎች አስደማሚ ውጤቶችን በማሳየት  ላይ መሆናቸውንና ለአብነት “ራቢት” በሚል ስያሜ የሚታወቀውን በመጥቀስ ድረ ገጹ ጽሁፉን አደማድሟል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here