የስቴፈን አበርክቶ

0
264

ስቴፈን ሃውኪንግ በ1942 እ.አ.አ በእንግሊዝ ሀገር በኦክስፎርድ ተወለደ፡፡ በጥቅምት 1959 በ17 ዓመቱ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በፊዚክስ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።    በካምብሪጅ ትሪኒቲ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ እ.ኤ.አ. መጋቢት 1966 በተግባራዊ ሂሳብ እና በቲዎሬቲካል ፊዚክስ በአጠቃላይ አንፃራዊነት እና ኮስሞሎጂ የትምህርት ዘርፍ ሦስተኛ ዲግሪውን አግኝቷል።

በትምህርት ሁል ጊዜ ለቀልዶች ዝግጁ የነበረውን ሃውኪንግ   ባለሙያዎች ሲገልጹት “እሱ ለትላልቅ እና ውስብስብ ነገሮች ብቻ የተነደፈ ልዩ የማሰብ ችሎታ አለው። ያም ሆነ ይህ  በአስተሳሰቡ እና በችግር አፈታት ላይ ቀድሞውኑ እንግዳ የሆነን ነገር የሚጠቁሙ የትዕይንት እጥረት የለበትም” በማለት ነው።

ሃውኪንግ በ22 ዓመቱ /በ1963/ በደረሰበት አካላዊ እንቅስቃሴ መገደብ/የጭንቅላት ሞተር ነርቭ/ በሽታ ከሁለት ዓመት በላይ መኖር እንደማይችል ተነግሮት ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በ1985 እ.አ.አ የመናገር ችግር ገጠመው፡፡ ይሁን እንጅ ስቴፈን በገጠመው የጤና ችግር ሳይደናገጥ እና ሀኪሞች ከምርመራ በኋላ በነገሩት ተስፋ ሳይቆርጥ እስከ ህልፈቱ በዊልቸር በመንቀሳቀስ እና ለሱ ተብሎ በተሠራ ኮምፒውተር በመታገዝ በርካታ የምርምር ውጤቶችን ለዓለም አበርክቷል፡፡

ሀውኪንግ በአንድ ወቅት ስለ አካላዊ የመንቀሳቀስ ውሱንነት ሲናገር “ምንም እንኳን አካሌ የመንቀሳቀስ ውስንነት ቢኖርበትም አዕምሮዬ ዓለምን በነፃነት ለማሰስ ይችላል…” ብሎ ነበር፡፡

ሃውኪንግ የእጅ ማብሪያ እና ማጥፊያን በመጨረሻም የአንድ ጉንጩን ጡንቻ በመጠቀም ንግግርን በሚፈጥር መሣሪያ መናገር ቻለ፡፡ የደረሰበትን የጤና ችግር በመቋቋም ባሳተመው “A Brief History of Time” የተሰኘው መጽሐፉ “በሰንደይ ታይምስ” የባለሞያዎች ዝርዝር ውስጥ ለ237 ሳምንታት ሥራው በበርካቶች በመነበቡ ቀዳሚው ለመሆን በቅቷል፡፡

ሃውኪንግ በገጠመው የጤና እክል ተስፋ ሳይቆርጥ በትምህርቱ ዘርፍ ባደረው ምርምር የሮያል ሶሳይቲ ባልደረባ ፣ የሕይወት ዘመን የጠፈር ሳይንስ አካዳሚ አባል እና የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛው የሲቪል ሽልማት የፕሬዝዳንት የነፃነት ሜዳሊያ ተሸላሚም ነበር። ከዚህ በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ2002 ሃውኪንግ በቢቢሲ ከ100 ታላቋ ብሪታንያ ሕዝብ ምርጫ 25ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

እ.ኤ.አ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓም በ76 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የፊዚክስ ሊቅ ስቴፈን ሀውኪንግ ከመሞቱ ስድስት ዓመታት ቀደም ብሎ የ70ኛ ዓመት ልደቱ በካምብሪጅ ውስጥ በሌዲ ሚቸል አዳራሽ ሲከበር  ታዋቂ የምርምር ሊቃውንት፣ የብሪታንያ የሮያል የሳይንስ አካደሚ ማርቲን ሪስ እና በፊዚክስ የኖቤል ተሸላሚው ሶል ፐርል ሙተር የክብረ በዓሉ ታዳሚዎች ነበሩ።

በጊዜው ስቲፈን ሀውኪንግ ባስተላለፈው በድምጽ በተቀረጸው መልእክት “የሰው ልጅ ከሚኖርባት ከተጎሳቆለችው ምድር ተነስቶ በሌሎች ፕላኔቶች መሥፈር ካልጀመረ የወደፊት ዕድሉ የጨፈገገ ነው። ለኑሮ በሌላ ፕላኔት ላይ ካላተኮርን በሚመጡት ሺህ ዓመታት በምድር ላይ የሰዎች ህልውና አስተማማኝ አይመስለኝም። ለመላው የዓለም ሕዝብ ስለፍጥረተ ዓለም ማስረዳት ተገቢ ነው። ርዕሰ ጉዳዩ ያሳደረው ፍላጎት ከነባቤ ቃል (ከቲዮሪ) የላቀ ነው። ፍጥረተ ዓለም እንዴት እንደሚሠራ ብታውቁ በሆነ ነገር ትቆጣጠሩታላችሁ” በማለት ነበር።

ብላክ ሆልስ እንዲሁም ሪላቲቪቲ/  የንፅፅር ሕግ/ በተሰኙ ሥራዎቹ የሚታወቀው የፊዚክስ ሊቁ ሃውኪንግ በርካታ ሳይንሳያዊ ፅሑፎችን አሳትሟል።

ገና በ22 ዓመቱ ሞተር ኒውሮን በተባለ በሽታ የተጠቃው  ሃውኪንግ በሽታው ሰውነቱን አሽመድምዶ ተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ እንዲውል ቢያደርገውም የጠፈር ምርምር  ፅንሰ ሃሳብን ለንፅፅር ሕግ እና ኳንተም ሜካኒክስ ጥምረት በማዋል የመጀመሪያው ሰው ለመሆን በቅቷል።   ሃውኪንግ ጨረር (ራዲዬሽን) የሚባለውን ፅንሰ ሃስብ በማፍለቅም ይታወቃል።

ስቴፈን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በመቅረብ በሚናገራቸው ንግግሮቹ የሚታወቅ ሲሆን ‘ቲየሪ ኦፍ ኤቭሪቲንግ’ የተሰኘው ፊልም የሊቁን የፍቅር እና ምርምር ሕይወት ቁልጭ አድርጎ እንዲያሳይ ተደርጎ ተሠርቷል።

እንግሊዛዊው የንድፈ ሀሳብ የፊዚክስ ሊቅ፣ የሥነ ትዕይንት /ኮስሞሎጂ/ ባለሙያ እና ደራሲው በመጨረሻው የሕይወት ዘመኑ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የቲዎሬቲካል ኮስሞሎጂ ማእከል የምርምር ዳይሬክተር ነበር። በ1979 እና 2009 መካከል በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሉሲያን የሂሳብ ፕሮፌሰር ነበረ።

ሃውኪንግ  በሳይንሱ ዘርፍ ላበረከታው በጥቁር ጉድጓዶች፣ በኮስሞሎጂ እና በብዛት በተሸጠው መጽሐፉ “የጊዜ አጭር ታሪክ” በሚለው ንድፈ-ሀሳቦቹ ይታወቃል። ለዚህ አበርክቶውም ሃውኪንግ የአዳምስ ፣ የኤዲንግተን እና የሂዩዝ ሜዳሊያን፣ የአንስታይን ሽልማትን እና የፕሬዚዳንታዊ የነፃነት ሜዳሊያን ጨምሮ ብዙ ሽልማቶችን አግኝቷል። የሃውኪንግ ሕይወት ተስፋ አለመቁረጥን፣ ስሜትን መከተል፣ ውስብስብነትን ማቃለል፣ ቀልደኝነትን መጠበቅ እና ተፅዕኖን በአዎንታዊ መልኩ መጠቀምን  ያስተምራል፡፡

ስቴፈን ሃውኪንግ ትዳር መስርቶ የሦስት ልጆች አባት መሆኑንም stiven-king-biogra እና neuroscience/scholar-awards በመረጃቸው  አመላክተዋል፡፡

(ሙሉ ዓብይ)

በኲር ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here