ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
135

በአብክመ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት1.የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ፣ሎት 2.የጽህፈት መሳሪያ ግዥ፣ሎት3.የጽዳት እቃዎች ግዥ፣ሎት4.ኤሌክትሪክና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ፣ሎት5.የፎሚጌሽን ሸራ ግዥ፣ሎት6.የመኪና ጎማና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ፣ሎት7.የኢንዱስትሪ የግብርና መገልገያ መሳሪያዎች/የመለኪያ መገልገያዎች መሳሪያ፣ ሎት 8.የኤፌሳር እና የሀይሉክስ መኪና የጥገና አገልግሎት ግዥ እና ሎት 9.ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአሸናፊው የሚገዙትን  መግዛት እና የሚሸጡትን መሸጥ ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው ፡፡
  2. በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት መያያዝ አለበት፡፡እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል/ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡እንዲሁም የጨረታ ሰነድ የገዛበትን የካሽ ሪጅስተር ደረሰኝ አብሮ ተያይዞ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ የገዛበትን የካሽ ሪጅስተር ደረሰኝ ያላያያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑ ይታወቅ፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት፣ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው እስከ 7ኛው ቀን አስከ 8፡00  ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ቅዳሜ የዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የንግድ ፍቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም ሎት 8. ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሲሆን በስሩ የተከፋፈለ ሎት ስላለው በተከፋፈለው ሎት መሰረት መርጦ መሙላትም ሁሉንም መሙላትም ይቻላል፡፡ሌሎችን ሎቶች ግን የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡
  12. አሽናፊው የአሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ሊያቀርብ እና ሊወስድ ነው፡፡ማንኛውም ወጭ አሸናፊ የሸፍናል፡የሚገዙትም ሆነ የሚሸጡት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡አሽናፊው የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡
  13. አሸናፊው የአሸነፈበትን ግዥዎች በፍትህ ውሉ ከተመረመረ/ከተመዘገበ/ የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል፡፡
  14. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  15. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 18 27 81 46 /09 18 27 83 96 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here