ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
119

በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. በቡሬ ከተማ ከሚገኘው መጋዝን ሎት 1. 10,000(አስር ሺህ)፣ ሎት 2. 5,000(አምስት ሺህ) ፣ ሎት 3. 25,000(ሃያ አምስት ሺህ ኩ/ል) ነጭ በቆሎ በሎት በመከፋፈል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፓስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ አስራ አንድ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  7. ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው 2በመቶ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ (ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማያያዝ አለበት)፡፡
  9. ሰብሉን አንስቶ የሚጨርስበት ጊዜ ለ5,000 /አምስት ሽህ/ ኩ/ል 15 ተከታታይ የስራ ቀናት 10,000 /አስር ሽህ/ ኩ/ል 30 ተከታታይ የስራ ቀናት 25,000/ሀያ አምስት/ ኩ/ል 60 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስጫኛ እና ሌሎች ወጭዎችን ገዥ የሚሽፍን ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587740640/1032 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here