ያልታሰበው ወሳጅ

0
244

በእንግሊዝ የባህር ዳርቻ ላይ ቆሞ የነበረ አይስክሬም አከፋፋይ ተሽከርካሪ ሳይታሰብ በተከሰተ ማእበል ተጠርጐ ወደ ባህር ከገባ ከ12 ሰአታት በኋላ በሰው ኃይል ተጐትቶ ሊወጣ መቻሉን ኤንዲ ቲቪ ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል፡፡

በእንግሊዝ ኮርንዌል በተሰኘው ታዋቂ የባህር ዳርቻ ቆሞ የነበረን አይስክሬም መጫኛ ተሽከርካሪ ድንገት የተከሰተ ማእበል ጠርጐ ሲያስገባው ድራማዊ ትእይንቱን በርካቶች መመልከታቸው በድረ ገጹ ለንባብ በቅቷል፡፡

በሀምሌ 7/2024 እ.አ.አ የተከሰተውን ሁነት በአካባቢው የነበሩ በትእንግርት መመልከታቸውንና ለማቆም መሞከራቸውን  ያስነበበው  የድረ ገጹ ፅሁፍ በተሽከርካሪው ውስጥ ምንም ሰው አለመኖሩን ነው በበጐ ጐንነቱ ያሰፈረው፡፡

ሀርሊን በተሰኘ ባህረ ሰላጤ ወይም ባህር ገብ መሬት ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ የተወሰደው ተሽከርካሪ በማግስቱ 3፡45 ጠዋት ተገፍቶ እና ተጐትቶ መውጣቱን ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ሁነቱ በተከሰተበት ወቅት በአካባቢው የነበሩ ጐብኚዎች እና ኗሪዎች በካሜራ ቀርፀው ያስቀሩት ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በመለቀቁም ብዙዎች እንዲመለከቱት አስችሏል፡፡

በርካቶችን ያስደነቀው ድንገተኛ ክስተት ማእበሉ ከቆመ ከሰዓታት በኋላ ፍፃሜ ማግኘቱን ያስነበበው ድረ ገጹ ተሽከርካሪው ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስበት ለባለቤቱ መድረሱንም ነው በማጠቃለያነት የሰፈረው – በድረ ገጹ፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here