ግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
134

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ለራሱ ለፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን እና አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት የተሸከርካሪ የመድህን ሽፋን ዋስትና፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች ጥገና እና በአውት ሶርስ የቢሮ የጽዳት አገልግሎቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. የአገልግሎት ግዥዎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
  8. በየዘርፉ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት አሸናፊ ሆኖ የሚመረጥ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እሰከ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሸጐ  በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here