ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የአሮጊ እቃዎች የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

0
152

የባሕር ዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ልዩ ልዩ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን የብረት ቧንቧ እና መገጣጠሚያዎች፣ የተለያዩ ዓይነት እና መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ HDPE PIPE እና መገጣጠሚያ፣ ጀኔሬተሮች፣ አገልግሎት የማይሰጡ ብስክሌቶች፣ የተሸከርካሪ ጎማዎች እና አሮጌ ተመላሽ መለዋወጫዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ በየሎቱ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የውሃ ቧንቧ እና መገጣጠሚያ (ብረት ነክ እቃዎች) እና ኤችዲፒ ቧንቧዎችና መገጣጠሚያ፣ ሎት 2. የተሽከርካሪ ጎማ የተለያየ መጠን ያላቸው ጎማ ነክ እቃዎች ሎት 3. አሮጌ የተለያዩ መፍቻዎች፣ ሎት 4. አሮጌ ወንበር እና ጠረንጴዛ፣ ሎት 5. አሮጌ ተሸከርካሪ ብስክሌቶች፣ የመኪና መለዋወጫ እና አዲስ መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 6. አሮጌ የውሃ ታንከር፣ ሎት 7. ኤሌክትሮኒክስ /ኮምፒውተሮች እና ፕሪንተሮች፣ ሎት 8. ጀኔሬተሮች እና ስዊች ቦርዶች ስለሚሸጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋውን አምስት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለ60 ቀናት በባሕር ዳር ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋ አምስት በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ማንኛውንም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በውሃ እና ፍሳሽ ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 210 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ኮፒ በተናጠል በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ባህርዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋናው መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 202 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት ውሃ እና ፍሳሽ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 202 በ15ኛው በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን የመጫረቻ ሰነድ  በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ የተገለፀው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ንብረቱ ካለበት ቦታ በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በዋጋ ማቅረቢያው በተዘረዘሩት ዕቃዎች ላይ በተናጥል ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይመረጣል፡፡
  10. ተጫራቾች በፖስታቸው ላይ ስም፣ ፊርማ፣ ስልክ ቁጥር መጻፍ እና በድርጅት ለሚወዳደሩ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት ባህር ዳር ከተማ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 320 50 79
  13. አድራሻ፡- ቀበሌ 08 የባሕር ዳር ከተማ ውሃና ፍሻስ አገልግሎት ጽ/ቤት ዋናው ቢሮ

የባሕር ዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here