ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
133

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት  ሎት 1. የፅዳት አገልግሎት፣ ሎት 2. የሆስፒታሉ ሠራተኞች ማመላለሻ  የመኪና ስርቪስ እና ሎት 3. የሆስፒታሉ ካፍቴርያ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ  አወዳድሮ  ካሸናፊ ድርጅቱ ጋር ለአንድ ዓመት  ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም  ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ፣ በዘርፉ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና በፅዳት አገልግሎት አዉት ሶርስ ለሚወዳደሩ የሥራ ልምድ አንድ ዓመት እና በላይ  የሰሩበት የሥራ ልምድ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት  ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያቁ /ቲን/ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን  የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን  ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዱ ጋር አያይዘው  ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር  መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/  እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር  ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን  ቢሮ ቁጥር 3  የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ  ምክንያት  በሚመለከታቸው የመንግሥት  ተቋማት  ያልታገዱ  መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ መሙያው ቅፅ ላይ ማንኛውንም የመንግሥት ግብር ያካተተ ሆኖ  የጨረታ ሰነዱ  በፖስታ ታሽጎ   የድርጅቱ ክብ  ማህተም፣ ፊርማ፣ ስም እና አድራሻ  በማስቀመጥ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ  ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለፅዳት አገልግሎት እና ለሠራተኞች ማመላለሻ የመኪና ሰርቪስ  ለሚወዳደሩበት ግዥ  የሚሞሉትን ጠቅላላ  ድምር ማንኛውንም ግብር ጨምሮ አንድ በመቶ፣ ለካፍቴሪያ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ  የክፍያ ትዕዛዝ  /ሲፒኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም በሆስፒታሉ ገቢ ደረሰኝ መሂ-1   ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ  ከፖስታው ውስጥ  አብሮ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው  ከታወቀ ለፅዳት አገልግሎት እና ለሰራተኞች ማመላለሻ የመኪና ሰርቪስ  ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ፣ ለካፍቴሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የውል ማስከበሪያ  ዋስትና  ማስያዝ  አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ  ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት  በ8፡30  ተጫራቾች  ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት  ሆኖ ባይገኙ  ግን ጨረታው  የማይስተጓጎል  ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች እቃውን /አገልግሎቱን/ በራሳቸው ወጪ እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በማምጣት ገቢ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here