የአብክመ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዓመታዊ የፅዳት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ ከ200‚000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መመሪያውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ አጠቃላይ የእቃዎችን ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ባሕር ዳር ከአብክመ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 009 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከሠነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን በማስፈርና በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቬሎፕ ዋና እና ቅጅ ሰነዶችን ለየብቻ በማሸግ ለአብክመ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 013 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 226 89 65 ባሕር ዳር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት