የአብክመ ሥራና ሥልጠና ቢሮ ለቢሮአችን ተሸከርካሪ መኪኖች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የመኪና የመለዋወጫ ዕቃ ፣ ሎት2. የመኪና ጥገና ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዓመታዊ ውል በመያዝ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታ ሰነዱ መሠረት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አይነት :- የመለዋወጫ ዕቃ ግዥ እና የጥገና ሥራ አገልግሎት፡፡
- በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ፡-
- አግባብነት ያለው ሕጋዊና በዘርፉ የተሰማሩ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ግዥው 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር G001 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በማንኛውም እቃ ግዥ ዋጋ 10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ ለአገልግሎት 3000.00/ሦስት ሽህ ብር/ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ ሁለት በመቶ የቅድመ ግብር ክፍያ ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ ሥራና ስልጠና ቢሮ፤ ቢሮ ቁጥር 01 00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ በደረሰኝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የጨረታው ሰነድ ላይ የተሞላውን የዋጋ ማሻሻል፣ መለወጥ ወይም ጨረታውን ሰርዣለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነተ የላቸውም፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፤ በ16ኛው ቀን በ14/12/2016 ዓ.ም 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሥራና ስልጠና ቢሮ ቁጥር G004 ይከፈታል:: በአስራ ስድስተኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የግዥውን አይነትና መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ /መረጃ/ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 53 95 / 058 226 53 97 መጠቀም ይችላሉ፡፡
- ቢሮው ለአሠራር ያመቸው ዘንድ ጨረታውን ሎት 1. በተናጥል፣ ሎት 2. ደግሞ በሎት ድምር የሚያወዳድር መሆኑን አውቃችሁ የዋጋ መሙያውን በጥንቃቄ ሞልታችሁ እንድታቀርቡ እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ፣ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ የሞሉትን የግዥ አይነትና የጨረታውን ዘዴ /ግልጽ ጨረታ/ በሚል ተጽፎ መቅረብ አለበት፡፡
የአብክመ ሥራና ሥልጠና ቢሮ