ከካንሰር ታዳጊዉ

0
142

በመኖሪያ ቤት አቅራቢያ አረንጓዴ ስፍራ ወይም የአትክልት ቦታ መኖር አካላዊ እንቅስቃሴን በማነሳሳት ለካንሰር መጋለጥን እና የዓየር ብክለት ተፅእኖን መቀነስ እንደሚያስችል ቴክኖሎጂ ዶት ኦርግ ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል::

በአውስትራሊያ ኩዊንስ ላንድ ዩኒቨርሲቲ የተመራ ጥናት  እንዳመላከተው በመኖሪያ ቤት አቅራቢያ አረንጓዴ ቦታ መኖር የአካል እንቅስቃሴን በማነሳሳት በውፍረት ሳቢያ የሚመጣ ካንሰርንና የዓየር ብክለትን መቀነስ ያስችላል::

ጥናትና ምርምሩን ያካሄዱ ባለሙያዎች ከ2006 እስከ 2010 እ.አ.አ በእንግሊዝ ስኮትላንድ እና ዌልስ ከ37 እስከ 73 ዓመት እድሜ ያላቸው ከ280 ሺህ በላይ ሰዎችን መረጃ ተንትነዋል::

ተመራማሪዎቹ እንዳስታወቁት መጠነ ሰፊ የተሰበሰበ መረጃን መሠረት አድርገው በተነተኑት መሰረት የጤና ክትትል ምዝገባ ባደረጉባቸው ስምንት ዓመታት ከ279 ሺዎቹ በ10 ሺዎቹ ላይ ከልክ ባለፈ ውፍረት ለካንሰር መዳረጋቸውን አረጋግጠዋል::

በናሙና ጥናት ከተሳተፉት በግል መኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ አረንጓዴ ስፍራ ያላቸው በካንሰር ወይም በጡት እና በሽንት ቱቦ ነቀርሳ የመያዝ አጋጣሚያቸው ዝቅተኛ መሆኑን ተገንዝበዋል::

አጥኚዎቹ በግልፅ የተረዱት እና የደረሱበትን እውነት እንዳሰፈሩት “በመኖሪያ ቤት አቅራቢያ ወይም ግቢ አረንጓዴ ስፍራ መኖሩ የአካል እንቅስቃሴ ለመስራት መልካም አጋጣሚ ይፍጥራል:: ቫይታሚን ዲ እንድናገኝ ያስችላል፤ ይህም ጥንካሬን እና በነቀርሳ መጠቃትን ያስቀራል” ሲሉ ነው ያደማደሙት::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here