በቻይና ቲያንጂን ከተማ በ2008 እ.አ.አ ግንባታው ተጀምሮ በ597 ሜትር ከፍታ 117 ፎቅ ላይ የቆመው ህንፃ በርዝመቱ ካልተጠናቀቁት በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል::
የህንፃው ባለንብረት ገንቢ “Goldin Group’’ የተሰኘ በመስኩ ልምድ ያላካበተ፣ ጀማሪ ዘርፉን የተቀላቀለ ቡድን ነበር:: የህንፃው ግንባታ ከተጀመረ ከሁለት ዓመት በኋላ ለመቆም ተገዶ ነበር – በታላቁ የምጣኔ ሀብት ውድቀት ምክንያት:: ከዚያም በ2011 እ.አ.አ እንደገና የግንባታ ስራው ቀጥሏል:: በዚያን ጊዜ ግንባታው በ2018 እስከ 2019 እ.አ.አ ባለው ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር- ሆኖም በ2015 እ.አ.አ ዳግም ግንባታው ሊቆም መቻሉን ነው ድረ ገጹ ያስነበበው::
ሰማይ ጠቀሱ ህንፃ ቢጠናቀቅ ከመሬት በላይ 128 ፎቅ ይኖረው ነበር – አሁን 117 ላይ ነው የቆመው:: በወቅቱ ህንፃው ሲጀመር እና በደረሰበት ደረጃ ላይ የግንባታ ቁሳቁስ ወይም ግብአት የዋጋ ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል:: በመሆኑም ባለንብረቶቹ ግንባታውን ለማጠናቀቅ አቅም እንዳጠራቸው ነው የተጠቆመው::
አሁን ላይ ያልተጠናቀቀው ህንፃ ቢጠናቀቅ ከዓለም አምስተኛ – ካልተጠናቀቁት በከፍታው አንደኛ ደረጃ መያዙን ነው ድረ ገጹ በማደማደሚያነት ያስነበበው::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም