የክረምት እረፍት ወቅት በተማሪዎች በጉጉት የሚጠበቅ ጊዜ ነው፤ ምክንያቱም ከተለመደው የትምህርት ጊዜ በተለየ ለማሳለፍ የሚያስችል አጋጣሚ ስለሆነ ነው። በዚህ ወቅት አንዳንድ ልጆች ጊዜያቸውን እንዴት በአግባቡ እንደሚጠቀሙበት ግራ ሊገባቸው ይችል ይሆናል። ወላጆች ግን የክረምት እረፍት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ለልጆቻቸው ማስገንዘብ እንዲሁም አስደሳች እና ፍሬያማ ጊዜ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት አስፈላጊ ነው።
እረፍት አስፈላጊ እንዲሆን የሚያደርጉት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
አዕምሮን ለማሳረፍ፦
ተማሪዎች በክረምት ወቅት ከትምህርት ቤት አዕምሯ እና አካላዊ ፍላጎት ወጥተው እረፍት እንዲያገኝ አጋጣሚ ይሰጣል። የመማር ፣ የማጥናት እና የማሰብ አቅማቸውን ለመጭው ትምህርት ዘመን እንደገና ለማዘጋጀት ፣ በበጋ የነበራቸውን ውጥረት ለመቀነስ እና በአጠቃላይ ደሕንነታቸውን ለማሻሻል እረፍት ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ለምርምር እና ለመማር የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ለመፍጠር የክረምት እረፍት ልጆች አዳዲስ ነገሮችን እንዲመረምሩ፣ አዳዲስ እንቅስቃሴዎችን እንዲሞክሩ እና በትምህርት ዓመቱ የማይቻሉ ይመስሏቸው የነበሩ አዳዲስ ችሎታዎችን እንዲማሩ አጋጣሚ ይሰጣል:: ለአብነት የሳይንስ ክበብ፣ የሒሳብ ውድድሮች፣ ስዕሎችን መሥራት፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ…ተጠቃሾች ናቸው።
የቤተሰብ ትስስርን ለማጠናከር
የክረምት የእረፍት ጊዜ ልጆች ረጅም ጊዜ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ አብረው ማሳለፍ የሚችሉበት፣ ዘመዶቻቸውን የሚጠይቁበት፣ የቤተሰብ ሕብረታቸውን የሚያጠናክሩበት እና ዘላቂ ትዝታ ለመፍጠር የሚችሉበትን ሰፊ ጊዜ ይፈጥርላቸዋል። የክረምት እረፍት ልጆች አዳዲስ ፍላጎታቸውን የሚመረምሩበት፣ አዳዲስ ችሎታዎችን የሚያዳብሩበት እና በሚወዱት እንቅስቃሴ የሚካፈሉበት ጥሩ ጊዜ ነው።
ክረምት ሕጻናት እና ታዳጊዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በአግባቡ ሊጠቀሙበት የሚችሉት ወቅትም ነው ማለት ይቻላል::
በንባብ ማሳለፍ፦
ማንበብ የቃላት አጠራርን እና የመረዳት ችሎታን ለማሻሻል፣ ነገሮችን ለመገንዘብ እና የማመዛዘን ችሎታቸውን ለማዳበር የሚያስችል ግሩም ጊዜ ነው። ወላጆችም ልጆቻቸው ዕድሜያቸውን የሚመጥኑ መጽሐፍትን እንዲያነቡ እና ባነበቡት ላይ እንዲወያዩ ሊያበረታቷቸው ይገባል።
ከቤት ውጭ አካባቢያቸውን ይጎብኙ፦
የክረምት ወራት ከቤት ውጭ ለመውጣት እና ተፈጥሮን ለመጎብኘት በጣም አስደሳች ጊዜ ነው::ወላጆች ልጆቻቸውን በእግር ጉዞ ፣ በጋራ ጉዞ ወይም ዘመዶች ባሉበት አዲስ አካባቢ ሊወሰወዷቸው ይገባል።
አዲስ ችሎታ መፍጠር፦
በክርምት እረፍት ወቅት እንደ ምግብ ማብሰል ፣ ስፓርት ወይም የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት የመሳሰሉ አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ጥሩ ጊዜ ነው።
በበጎ ፈቃድ መሳተፍ፦
በበጎ ፈቃድ ሥራ እረፍትን ማሳለፍ እርካታ የሚገኝበት መንገድ ነው::በዚህም ልጆች በማኅበረሰባዊ አገልግሎት ፕሮጀክቶች እንዲሳተፉ ወይም በአካባቢው በሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ ፈቃደኛ ሠራተኛ ሆነው ሌሎችን እንዲያግዙ እና ልምድ እንዲወስዱ ወላጅ ማበረታታት ይገባዋል።
ታዲያ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የሚፈልጉትን የእረፍት ማሳለፊያ ከተነጋገሩ በኋላ እንደ ወላጅ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸው በርካታ ነገሮች አሉ::ከነዚህም ውስጥ፤
አስቀድሞ እቅድ ማውጣት
የክረምት እረፍት ከመጀመሩ በፊት ከልጆች ጋር ቁጭ ብሎ ሊሠሯቸው የሚፈልጓቸውን እንቅስቃሴዎች በዝርዝር መጻፍ ያስፈልጋል።
የመዝናናት እና የተለየ ነገር ለማድረግ የሚያስችል ልምድ (በየጊዜው የተለያየ) ለልጆችዎ ይፍጠሩ፦
ልጆች በበጋ እረፍት ወቅት ዘና እንዲሉ እና እንዲዝናኑ መፍቀድ አስፈላጊ ቢሆንም አንድ የተለየ በየጊዜው የሚያደርግ ማነቃቂያ ተግባር መፍጠር ትርጉም ባለው እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ሊረዳ ይችላል።
የፈጠራ ችሎታን አበረታቱ ፦
ወላጆች ልጆች እንደ ሥዕል ወይም መጻፍ ባሉ የፈጠራ ሥራዎች እንዲካፈሉ ማበረታታት ያስፈልጋል::ይህ ሲሆን የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እና ሐሳባቸውን እንዲያሳድጉ ሊረዳቸው ይችላል።
“የክረምት እረፍት” የናፍቆት እና የማሰላሰል ስሜትን ያሰፍናል። ወላጆች በክረምት ወቅት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ፤ እናም ልጆች በማንበብ ፣ በማጥናት ወይም ማጠናከሪያ ትምህርት በመውሰድ ቢያሳልፉም በየዓመቱ አንዴ የሚመጣውን ክረምት በጉጉት እንዲጠብቁ የሚያደርግ ወቅት በመሆኑ የደስታና የተለየ ስሜት መፍጠር እንዲችል ማድረግ ከወላጆች ይጠበቃል::
ወላጆች ልጆቻችሁ ጥሩ የክርምት እረፍት እንዲያሳልፉ አስፈላጊ የሆነው በርካታ ምክንያቶች ስላሉት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች በበጋ ከተማሩት የትምህርት ጥናት ዘርፍ ተግባራዊ የሥራ ልምድ እንዲያገኙ እድል ያፈጥራል። ይህም ወደፊት የሥራ ሕይወታቸው ምን ሊመስል እንደሚችል ለመረዳት ያስችላል::
በተጨማሪም ተማሪዎች እረፍት መውሰዳቸው ዘና እንዲሉ ያስችላቸዋል። ይህም አጠቃላይ ደህንነታቸውን የአዕምሮ ጤንነታቸውን ለማሻሻል በጣም ይረዳል።
ከዚህም በላይ በእረፍት ጊዜ ተማሪዎች አዳዲስ መዳረሻዎችን እንዲቃኙ፣ በመዝናኛ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ እና የተለያዩ ባህሎችን እንዲለማመዱ ዕድል ይሰጣል። ይህ ደግሞ የማሰብ አድማሳቸውን ለማስፋት እና የግል ዕድገታቸውን ለማጎልበት ያስችላል።
አብዛኛውን ጊዜ በእድሜ ከፍ ያሉ ታዳጊዎች ይሄንን ወቅት በመጠቀም ራሳቸውን በገንዘብ ለመደገፍ ሲሉ በአቅማቸው ሥራ ስለሚፈልጉ የእረፍት ጊዜ ተማሪዎች በገንዘብ ረገድም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
https://typeset.io//እናpodarsmarterschools.com ከተባሉት ድረ ገጾች ያገኘናቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በማንበብም ፣በመሥራትም ሆነ ቤተሰብን በመጠየቅ ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ መክረዋል::
(ማራኪ ሰውነት)
በኲር ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም