ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
121

የባሕር ዳር ከተማ በአፄ ቴወድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ ዓለም ሆስፒታል አግልግሎት የሚውል ሎት 1. የግቢ አጥር ግንባታ ሎት 2. የጥበቃ አገልግሎት፣ ሎት 3. የታካሚ የምግብ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና ማቅረብ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ሰርተፊኬት የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስድስት ወር ያላለፈው ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ የምዝገባ ስርተፊኬት (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. ለግንባታ ጨረታ የሥራ ዘርፍ ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ፈቃድ ያላቸውን ደረጃ-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑትን የሚያካትት መሆን አለበት፡፡
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መያዝ አለበት፡፡ የውል ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የመጫረቻ ሰነዱ በሁለት ፖስታ ዋና እና ቅጅ(ኮፒ) በማሸግ ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በአየር ላይ የሚውልበት ለግንባታው ጨረታው ለ21 ተከታታይ ቀናት ለምግብ አቅርቦት እና ለጥበቃ አግልግሎት ጨረታው ለተከታታይ 15 ቀናት ይሆናል፡፡
  10. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. የእስፔስፊኬሽኑን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይቻላል፡፡
  14. አሸናፊው የሚለየው የግንባታው በጠቅላላ ድምር አርቲማቲክ ውጤት ዝቅተኛ ዋጋ ሲሆን የምግብ አቅርቦት እና የጥበቃ አገልግሎት በጠቅላላ ሎት ድምር ውጤት ነው፡፡ የመወዳደሪያ ዋጋው ቫትን ይጨምራል፡፡
  15. በጨረታ ወቅት ጨረታው ውድቅ ቢሆን ተጫራቾች የሚያወጡትን ወጭ ሆስፒታሉ አይሸፍንም፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ አዲስ ዓለም ሆስፒታል ቁጥር 08 ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 34 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አዲስ ዓለም ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here