ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
114

በአብክመ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰቆጣ ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት ለሕግ ታራሚዎች ምግብ የሚውሉ 1. የተለያዩ የእህል፣ የጥራጥሬና የአገዳ እህል፣ 2. የፊኖ ዱቄት  እና 3. በርበሬና ቅመማ ቅመም  ለአንድ ዓመት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የወጣ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ከ50,000.00 /ከሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በግልፅ በሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ለምግቡ የሚያስፈልጉ የእህልና የጥራጥሬ እንዲሁም የፊኖ ዱቄት፣ በርበሬ እና ቅመማቅመም ዓይነቶችን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ የመሸጫ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ6/12/2016 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የተለያዩ የእህል የጥራጥሬና የአገዳ እህል ውል ማስከበሪያ ለአንድ ዓመት ተይዞ የሚቆይ 60,000.00/ስልሳ ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  11. ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ለፊኖ ዱቄት ውል ማስከበሪያ ለአንድ ዓመት ተይዞ የሚቆይ 30,000.00 /ሰላሳ ሽህ ብር/ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  12. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ለበርበሬ እና ቅመማ ቅመም ውል ማስከበሪያ ለአንድ ዓመት ተይዞ የሚቆይ 20,000.00 / ሀያ ሽህ ብር/ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በቀን 21/12/2016 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30  ይከፈታል፡፡
  15. መሥሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 01 14 ወይም 09 92 04 68 95 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ:- ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰቆጣ ማረሚያ ቤት ቀበሌ 01

የሰቆጣ ማረሚያ ቤት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here