ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
201

በአብክመ በደ/ጎን/አስ/ ዞን የጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ኃ.የተወሰነ ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ለዩኒዬኑ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጨረታዎችን በሎት ከፋፍሎ እንዲወጣ ሎት 1. የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4. የተለያዩ ሕትመቶች፣ ሎት 5. የተለያዩ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች /ፈርኒቸር/፣ ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና ሎት 7. የህንፃ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት  መስፈርቱን  የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ቲን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ሲፒኦ ከታወቀ ባንክ በጥሬው ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  6. ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት አቅርቦት አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኝት ይችላሉ፡፡
  8. መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች በጥንቃቄ በፖስታ ታሽጎ ጉና ዘር ብዜትና ግብይት ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን በሚገኝበት ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደብረተታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ከሚገኘው ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ስዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ10ኛው ቀን 2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ   ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የመክፈቸው እለት የሕዝብ በዓል /ካላንደር/ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ በጥንቃቄ በማሸግ የድርጅቱን ክብ ማህተም በዩኒየኑ ግዥ ፋይናስ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ይህ ማስተዋቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  12. የበለጠ መረጃ ለማግኝት በስልክ ቁጥር 09 30 70 99 26/ 09 79 26 13 56/ 09 18 21 87 40/ 09 18 01 85 02 መደወል ይችላሉ፡፡
  13. ከጉና የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ደብረታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ቡና ባንክ ላይ ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  14. ለእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ማግኝት ይችላሉ፡፡
  15. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ዩኔየኑ የመጨመርም ሆነ መቀነስ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ዩኔየኑ አሸናፊውን የሚለየው እንደ አስፈላጊነቱ በነጠላ ወይም በጠቅላላ ዋጋ ድምር ውጤት ይሆናል፡፡ በዩኔኑ ግዥንና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም የሆናል፡፡

የጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here