በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለ2017 ዓ.ም በካፒታል በጀት በማ/ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ የኖራ ማቃጠያ፣ መሃዝን፣ ላብራቶሪ፣ የጥበቃ ቤት፣ መፀዳጃ ቤት እና አጥር የያዘ ፋብራካ/ኘሮጀክት ግንባታ ሁሉንም ችሎ የሚሠራ ኮንትራክተር ደረጃ ሰባት እና ከዚያ በላይ የሆነ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በጠቅላላ ዋጋ /በሎት/ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የብቃት ማረጋገጫ በዘርፋ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ እና ለእያንዳንዱ ሰነድ በፖስታ ኦርጅናል ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በነፃ ዋጋ ላይ የተመሰረተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱን 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የግንባታ ሥራው ከተጀመረበት ቢበዛ በ220 የሥራ መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርኘራይ ለተደራጁ ወጣቶች የሥራ እድልን ለማስፋትና ለማበረታታት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 27/2009 ዓ.ም ላይ የተመሰረተ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለ90 ቀናት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የቴክኒካል መመዘኛ መስፈርቱን የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ21ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ሙሉ በሙሉ ማንበብና ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 202 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 97 04 በሥራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የአብክመ ሴ/ህ/ጉ/ቢሮ ባሕር ዳር ቀበሌ 16 ግብርና ምርምር ቢሮ ፊትለፊት ካለው ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 እንገኛለን፡፡
የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ