በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሸዶች የሚያገለግል መካከለኛ ቮልቴጅ ኬብል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ገንዘብ ያዥ ክፍል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 6,000.00 /ስድስት ሺህ ብር/ ብቻ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መሥሪያ ቤቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በማሸግ አረጋዊያን ህንጻ ከሚገኘው ኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የካሌንደር ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብከመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ግ/ፋ/ንብ/ አስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ በ21ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፤ ሆኖም 21ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በድምር ዋጋ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ኬብሉን በስፔስፊክሽኑ መሰረት መሆኑን በባለሙያ ካረጋገጠ በኋላ ከኮርፖሬሽኑ ንብረት ክፍል በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ግ/ፋ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 47 67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብከመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን