በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሎት 1. ተኝተው ለሚታከሙ በሽተኞች ምግብ የሚያቀርብ ለአንድ ዓመት ከቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ ሲሆን፣ ሌሎችን በተናጠል የሚታዩ ደግሞ የህክምና መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ እና የጽዳት እቃ የሆኑትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ፤ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ካርድ/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ዓመታዊ የምግብ አቅርቦቱ ከ200,00.0 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ስለሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እንዲሁም ለሌሎች ጨረታዎች አቅርቦቱ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግሥት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መሥሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 (ሃምሳ ብር) ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- በዚህ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልገው ጨረታውን ላወጣው መሥሪያ ቤት በጽሑፍ ወይም በፋክስ ቁጥር 058 661 02 64 ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 03 30 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መሥሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሑፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድና ዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠየቀው ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ 4,000.00 (አራት ሽህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል