ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
166

የጨረታ ቁጥር 002/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ በመደበኛ  በጀት ሎት 1. ግራናይት አለሙንየም  እና ሴራሚክ፣  ሎት 2. የጅኦሎጅ እቃዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የከበሩ ድንጋይ ማዋቢያና መስቀመጫ እቃዎች፣ ሎት 5. የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 6. የጽሕፈት መሳሪያ እና ሎት 7. የጽዳት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

  1. በዘርፉየታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የግዥው መጠን 200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የእቃው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ  ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ እና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ የሚወዳደሩበትን እቃ ሁለት በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀ እና ኢነርጅ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 27 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 27 በ8፡30  ላይ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያ ቀን 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 78 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ ውሃ እና ኢነርጅ  ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here