በደብረ ታቦር ከተማ የልደት ኃ.የተወሰነ የህብረት ሥራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን በታች ጋይንት ወረዳ በአርብ ገበያ ከተማ ለሚያስገነባው ቤዝመንት + 3 ህንፃ የሚሆን የሃገር ውስጥ ሴራሚክ 60X60፣ የሃገር ውስጥ ሴራሚክ 20X30፣ የበር እና መስኮት LTZ ቱርክ ባለ 38 ሚሜ፣ D ቱርክ የበርና የመስኮት ፍላት ኢሚቴሽን፣ የበርና መስኮት ሰረገላ ቁልፍ ጣሊያን፣ ባለ 5 ሚሜ አንፀባራቂ መስታዎት የህንፃ መሳሪያ አቅራቢ ድርጅቶች ፈቃድ ካላቸው መካከል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች መረጃቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫና የእቃውን ብዛት ዩኒዬኑ ካዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ልደት ዩኒዬን ዋናው ቢሮ ቁጥር 1 ላይ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር / በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው ባንኮች ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን ነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ልደት ዩኒዬን ዋናው መሥሪያ ቤት ላይ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ፣ ስም፣ አድራሻ በመጻፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ ከጨረታ ሳጥኑ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ብቻ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እሰከ 11፡30 ድረስ የሚቆይ ሁኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የህዝብ በዓል ወይም ካላንደር ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ ግንባታው ከሚያሠራበት ታችጋይንት ቅርንጫፍ ድረሰ ማቅረብ አለበት፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ስለጨረረታው ዝርዝር መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 18 19 59 73/ 09 18 21 74 87 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ልደት ኃ.የተወሰነ የህብረት ሥራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን