ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
157

በሰሜን ጎጃም ዞን በአዴት ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈትና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተፈላጊ መረጃዎች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ስንጋብዝ፡-

በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ተነባቢ የሆነ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ ከፍለው አዴት ከተማ አስ/ገን//ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ  ለኤሌክትሮኒክስ እና ለጽሕፈት መሳሪያ ለእያንዳንዱ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በቢድ ቦንድ ወይም በክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመሥሪያ ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር የሚያስገባ እና ዲፖዚት ስሊፕ ማቅረብ የሚችሉ ወይም በመሥራያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ የሚያደርግ እና የገቢ ደረሰኙን  ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡

አሸናፊ ድርጅቱ  የውል ማስበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ አስር በመቶ ዋስትና በቢድ ቦንድ ወይም በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ የሚችሉ እና ዲፖዚት ስሊፕ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በፖስታ በማድረግ የድርድቱን ማህተም በመምታት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል በመሆኑ በመንግሥት የሥራ ሰዓት እስከ 11፡00 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሰነዱን በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ድረስ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00  ታሽጐ በ3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡

የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ወይም እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 338 00 20 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 19 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጽ/ቤቱ እንደ ሁኔታው አይቶ  የሎት ግዥውን ሃያ በመቶ የመቀነስ እና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ የአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- እኛ ከሸጥንላችሁ ሰነድ ውጪ በራሳችሁ መሙላት፣ በፍሉድ ማጥፋት፣ ሥርዝ ድልዝ፣ በራስ ስፔስፊኬሽን ዋጋ መሙላት እና ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡

የአዴት ከ/አስ/ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here