የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በ2016/2017 የምርት ዘመን የሚባዛን የተለያዩ ሰብሎች ምርጥ ዘር ከተመረተበት አስከ ሚከማችበት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም፣ በተጨማሪም ኬሚካል እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የትራክተር እና የኮምባይነር መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ ዘይቶችና ቅባቶች፣ ሚዛን (የህንፃ መሳሪያ)፣ የሞተር ሳይክል እቃዎችን ለመግዛት እና የተለያዩ ለዘር የማይውሉ ሰብሎች፣ ብጣሪዎች እና ያገለገሉ ጆንያዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-
የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር/ ቢሮ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግሥት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የመኪና ባሌቤትነት ማረጋገጫ እና የመጫን ችሎታ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪናዎች ያሉትና የመኪናዎችን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ከዋናው ጋር የተረጋገጠ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ሲጠየቅ ዋናውን ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የባለቤትነት ማረጋገጫው በውክልና በ2016 ዓ.ም የተሰጠ ሆኖ ውክልናው አግባብ ባለው የፍትሕ አካል የተረጋገጠ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚጓጓዘውን ምርጥ ዘር አይነት፣ መጠን እርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርፕራይዙ ዋና መሥሪያ ቤት /ባሕር ዳር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸው፡፡
ያገለገሉ ጆንያዎችና ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርብ አይገደድም፡፡
ግዥውን ባሕር ዳር ዋናው መሥሪያ ቤት መጋዘን መድኃኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ሰብሎችን በተመለከተ ባሕር ዳር፣ ኮምቦልቻ፣ እንጅባራ፣ ብር ሸለቆ እና ደብረ ብርሃን የሚገኙ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ይመልከቱ፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ በአለ በጅምላ ግቢ ውስጥ በሚገኘው በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ 10ኛው ቀን (ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን) በ8፡30 ይከፈታል፡፡
ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀው ውስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ ሃምሳ በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 /09 18 01 69 35 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ