በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለ2017 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ አቅርቦቶችን እና አገልግሎቶችን በመደበኛ በጀት፣ በተራድኦ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሕትመት ሥራ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህክምና ግብዓቶች አቅርቦት፣ የህ/መሳሪያዎች እና የጀኔረተር ጥገና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ እና ተከታታይ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የህክምና ግብዓት እና የህ/መሣሪያ ጥገና በነፃ ማግኘት ሲችሉ ሌሎችን ግን ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ 50.00 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ ከነ ቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ኢንስቲትዩቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በ16ኛው ቀን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋቱ 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 3፡35 ላይ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረብያ ሰነድ ሆነ ፖስታ ላይ ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ሞልቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ኢንስቲትዩቱ የጨረታ አሸናፊው ከተለየ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት ሃያ በመቶ በመጨመር ወይም በመቀነስ ውል ይዞ የማስቀረብ መብት ይኖረዋል፡፡
የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ምድብ በድምር ዋጋ ይሆናል፡፡
ጨረታው በሎት ስለሆነ ተወዳዳሪዎች የገዙት ሰነድ ላይ ሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በሥራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የሚሰበስበው ሁለት በመቶ ዊዝ ሆልድ ብቻ ነው፡፡
አድራሻ፡- ፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ጎን
የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት