ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
142

የምሥራቅ ጐጃም አስ/ዞን የእነማይ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት  በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ከመደበኛ እና ከ5028 በጀት ላይ ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3. የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እቃዎች፣ ሎት 4. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 5. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 6. የሕትመት ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዝርዝር መረጃውም በጨረታ ሰነዱ ተካቷል፡፡ በጨረታው ለመሣተፍ መሟላት የሚገባቸው፡-

ዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ከሎት 2 በስተቀር የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የተመዝጋቢ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለሁሉም ሎቶች ከጨረታው አሸናፊ ላይ ሁለት በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለእያንዳንዱ ሎቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ከሎት 1. እስከ ሎት 3. 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከሎት 4. እስከ ሎት 6. ለእያንዳንዳቸው 50.00 /ሃምሳ ብር/  ብቻ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ለሎት 1. 5,000.00 /አምስት ሽህ ብር/ ብቻ፣ ለሎት 2. እና ለሎት 3. ለእያንዳንዳቸው 10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ ብቻ፣ ከሎት 4. እስከ ሎት 6. ለእያንዳንዱ 200.00 /ሁለት ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/፤ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመሥሪያ ቤታችን መሂ-1 ገቢ ማደረግ አለባቸው፡፡

ከሎት 1. እስከ ሎት 6. ላሉ ግዥዎች አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡

ከሎት 1-6 አሸናፊ ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት እ/ወ/ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡

ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30  ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆኑ ነገሮች መኖር የለበትም፤ ካለም ተጫራቹ ፖራፍ ማድርግ አለበት፡፡ በጨረታ ሰነዱ እና በፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡

በባለሙያ የሚረጋገጡ እቃዎችን በባለሙያ እየተረጋገጡ የምንረከብ መሆኑ እና አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈባቸውን እቃዎች በእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሥር ባለ ንብረት ክፍል ድርስ አስፈላጊውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

እያንዳንዱ ሎት መሥሪያ ቤቱ አሸናፊውን የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች በየሎት ምድቡ የቀረቡትን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ /ውድቅ/ ይሆናሉ፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል የጨረታ ማስከበሪውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና በፖስታው ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ከሎት 1-6 ላሉ የሎት ምድቦች ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሣይቀይር ከእቃው ከጠቅላላ መጠን ላይ ሃያ በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ዋጋ መሙላት ሲኖርበት በራሱ ዋጋ መሙያ ከሞላ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 00/ 058 665 00 08 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእነማይ ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here