ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
108

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1.  የተለያዩ የመድኃኒት አይነቶችን ለስድስት ወራት እና ሎት 2.  የተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦትን ለአንድ ዓመት  ውል በመያዝ  ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም  ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

በዘርፉ ሕጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የመንግሥትን ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ያላቸው እና በመድኃኒት አቀርቦት ላይ  የሚጫረቱ ተጫራቾች ሜዲካል ሰርተፊኬት ያላው፡፡

የግብር ከፋይነት መለያቁ /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡

የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ  ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን  የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ  ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን  ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዱ ጋር አያይዘው  ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡

ስለጨረታው  አጠቃላይ ዝርዝር  መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር  ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3  የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ከዚህ በፊት  በልዩ ልዩ  ምክንያት  በሚመለከታቸው የመንግሥት  ተቋማት  ያልታገዱ  መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ መሙያው ቅፅ ላይ  ማንኛውንም   የመንግሥት ግብር ያካተተ ሆኖ  የጨረታ ሰነዱ  በፖስታ ታሽጎ   የድርጅቱ ክብ  ማህተም፤ ፊርማ፤ ስም እና አድራሻ  በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ  ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡

ተጫራቾች  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለመድኃኒት 10,000.00 /አሰር ሽህ ብር/ እና የተኝቶ ታካሚዎች ምግብ አቅርቦት 30,000.00 /ሰላሳ ሽህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ  የክፍያ ትዕዛዝ  /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም በሆስፒታሉ ገቢ ደረሰኝ መሂ-1   ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ  ከፖስታው ውስጥ  አብሮ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች  አሸናፊ መሆናቸው ከታወቀ ለመድኃኒት 30,000.00 /ሰላሳ ሽህ ብር/  እና ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት 400,000.00 /አራት መቶ ሽህ ብር/ የውል ማስከበሪያ  ዋስትና  ማስያዝ  አለባቸው፡፡

ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት  አየር ላይ  ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት  በ8፡30  ተጫራቾች  ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት  ሆኖ ባይገኙ  ግን ፕሮግራሙ  የማይስተጓጎል  ይሆናል፡፡

ተጫራቾች እቃውን /አገልግሎቱን/ በራሳቸው ወጪ እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በማምጣት ገቢ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ሆስፒታሉ አሸናፊውን የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል  ይሆናል፡፡

መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን  በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here