ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
126

የአዊ ብሔ/አስ/ንዘብ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ  ሎት 1. የጽሕፈት መሣሪያና ተዛማጅ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ሎት 2. የፕሪንተር፣ ፋክስና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት 3. የጽዳትና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስና ሌሎች ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 5. በክርና ከሽቦ የተሠራ የመኪና ጎማ፣ ሎት 6. ኢምፖርትድ ፈርኒቸር እና ሎት 7. የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ  መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ሠርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የሚገዛው የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር ሁለት በመቶ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሥሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ አዊ ብሔ/አስ/ገ/ኢ/ትብ/ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 በማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡

የማወዳደሪያ ሥርዓቱ የደንብ ልብስ በነጠላ ዋጋ አይተም ነው፤ በደንብ ልብስ የሚወዳደሩ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤ ከደንብ ልብስ ውጭ ሌሎች እቃዎች በሎት /በጥቅል ዋጋ ነው፡፡

የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሽግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በአዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግሥት ግብር/ታክስ/፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጭዎች ማካተት ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ በማስፈተሽ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 227 00 66 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዊ ብሄ/አስ/ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here