ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
126

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካይነት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያ እና ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየ አንዳንዱ ሎት 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 ከ18/02/2017 ዓ/ም እስከ 02/03/2017 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ  ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በመክፈል ደረሰኙን በፖስታ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን በተከታታይ ቀናት እስከ 03/03/2017 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 03/03/2017 ዓ/ም በ16ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ለጨረታው መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች ባሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታውን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለው፡፡

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማንኛውም ተጫራች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ዕቃውን በፍጥነት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የመኪና መለዋወጫ እቃ በለቀማ የሚገዛ ሲሆን የጽሕፈት መሳሪያ ግን በሎት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማንኛውም ተወዳዳሪ የጽሕፈት መሳሪያውን  ጽ/ቤቱ ያቀረበውን ናሙና በትክክል በማየት መወዳደር ይኖርበታል፡፡

ጨረታው የሚከፈተው ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የካላንደር በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ  ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ከዚህ በፊት በየትኛውም ደረጃ በነበራቸው የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም፡፡

የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here