ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
174

የጨረታ ሰነድ ቁጥር kfw/01/2017

በጀርመን መንግሥት የልማት ትብብር ባንክ /KfW/ የደቡብ ወሎ ደን ልማት እና ብዝሀ ህይወት ሀብት ጥበቃ ፕሮጀክት የ2016 በጀት ዓመት ሂሣብን በሰርቲፋይድ ቻርተርድ አካውንታንት፣ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግና የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ  ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ የሚሰጡ ከሆነ)፡፡

የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው በአብክመ የአካባቢ፣ ደንና  ጥበቃ ባለስልጣን   ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡

ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በ60.00 /ስልሳ ብር/ በመግዛት ከድርጅቱ በመውሰድ መጫረት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ”፣ “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የባንክ ሲፒኦ /ቢድ ቦንድ/” በማስያዝ በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ  ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተ.ቁ 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ውስጥ  ግዥ ቢሮ  ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

የጨረታ ሳጥኑ በጨረታ መዝጊያው ቀን ከጠዋቱ በ3:00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ3:30 በድርጅቱ ግዥ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

200,00.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

ቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

ከ20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ለሆኑ ግዥዎች ቫቱን በግማሽ በመቶ ቢሮው የሚያስቀር መሆኑን አናሳውቃለን፡፡

መሥሪያ ቤቱ አሸናፊውን ድርጅት በነጠላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ   የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 62 06 ወይም 09 18 18 73 68 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአብክመ አካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here