ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

የባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለመደበኛ እና ለማታ ት/ት ሰልጣኞች ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የህንፃ ግንባታ ማሰልጠኛ ዕቃዎች፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች ማሰልጠኛ ዕቃዎች፣  ሎት 3 የጽዳት ማሰልጠኛ ዕቃዎች፣ ሎት 4 የልብስ ስፌት፤ የጨረቃ ጨርቅ  እና የቆዳ ውጤቶች ሎት 5  የኤሌክትሪክሲቲ ማሰልጠኛ ዕቃዎች፣ ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ እና ኤሌክትሪክሲቲ ማሰልጠኛ ዕቃዎች እና  ሎት 7 ብረታ ብረት ማሰልጠኛ ዕቃዎች  በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

ጨረታው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የማይመለስ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ  አለባቸው፡፡

ጨረታውን ሲሞሉ በፖስተው ላይም ሆነ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅቦዎታል፡፡

ጨረታውን በሚሞሉበት ጊዜ በጨረታ ዋጋው ማቅረቢያ ላይ ምንም አይነት በነጠላም ሆነ በጥቅል ዋጋው ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡

ጨረታውን በሚሞላበት ጊዜ በተጠየቀው መለኪያ መሰረት መሙላት ይጠበቅቦታል፡፡

እያንዳንዳቸውን እቃ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ3 ወር የሚቆይ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወደደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ በኮሌጁ ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ በጥቃቅን የሚወዳደሩ ከሆነ ከኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ጨረታው የሚዘጋበት ቀናት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ኮሌጁ ጨረታውን በጥቅልም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡

በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ንብረቱን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ በሙያተኛ በማረጋገጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር 058 218 05 74 እና ፋክስ ቁጥር 058 218 05 78 ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡

ባህር ዳር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

አባይ ማዶ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here