በአብክመ ማረ/ቤቶች ኮሚሽን በደ/ጎ/ዞ/ማረ/ቤቶች መምሪያ አዲስ ዘመን ማረ/ቤት አስ/ጽ/ቤት የህግ ታራሚዎች ምግብ እና ምግብ ነክ የሚውሉ ሎት 1 ጤፍ፣ በቆሎ፤ ሩዝ፤ ሎት 2 የባቄላ ክከ ተቀምሞ የተፈጨ በርበሬ፣ ሎት 3 የዳቦ ፊኖ ዱቄት፣ ሎት 4 የዳቦ ማንኳፈፊያ፤ የምግብ ጨው፣ ሎት 5 የምግብ ዘይት፣ ሎት 6 የማገዶ እንጨት በግልፅ ጨረታ ግዥ ዘዴ ከአቅራቢዎች መካከል በሎት ድምር አወዳድሮ መግዛት (ማሰራት) ይፈልጋል፡፡ ስስሆነም፡-
በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት (የቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
የመግዛት አቅም ቫት ከማይጠየቅባቸው ምግብና ምግብ ነክ ውጭ ባሉት ግዥዎች ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ለሆናችሁ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ከ1-3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ የእያንዳንዱን ሎት ለየ ብቻ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከአቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ ሎት 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሎት 2 ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ፤ ሎት 3 ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)፤ ሎት 4 ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)፤ ሎት 5 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፤ ሎት 6 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማቅረብ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ውል ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ ዋጋ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥረ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2502/2017 ዓ.ም እስከ 8/03/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የመጫረቻ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት 50.00 (ሃምሳ ብር) ብቻ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ እስከ 11፡30 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ቅጽ ላይ የሞሉትን ዕቃ ግዥ ስፔስፊኬሽን እና ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ያለምንም ሥርዝ ድልዝ ተሞልቶ በቀን 10/3/ 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ እስከ 3:25 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት በ3፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ሰዓት በ4፡00 ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም በሌሉበት ይከፈታል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያው ውድድር የሚካሄደው በሎት ስስሆነ በሎቱ የተጠየቀው ዕቃ፣ ሁሉም በትክክል መሞላት አለባቸው፡፡ አሸናፊዎች የሞሉት ዕቃ ዋጋ አያንዳንዱ ዋጋ ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው፡፡
ከላይ በሎት 3 ፣ ሎት 4 ፣ ሎት 5 ፣ ሎት 6 ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉትን ማለትም ሎት 1 እና 2 በጨረታ መክፈቻ ጊዜ ተወዳዳሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ናሙና ማቅረብ አስባቸው፡፡
የጨረታ አሸናፊው የአሸናፊነት ጥሪው ከደረሰው ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአሸነፉበት የመጫረቻ ዋጋ መሰረት የውል ማስከበሪያውን በማሲያዝ ውል መውሰድ የሚችሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በዕቃ ወይም አገልግሎት ግዥው ላይ አሳማኝ ምክንያቶች ካሉ እና መ/ቤቱ ካመነበት እስከ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
ከላይ በሎት ምድብ የተጠቁት ግዥዎች አቅርቦት ወጪ በአቅራቢው ሲሆን አዲስ ዘመን ማረሚያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ሰበሰበ መረጃ በቢሮ ስልክ 058 444 09 71 (00 31 (09 18 44 14 28፡፡ ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
አዲስ ዘመን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት