ለሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፍ/ቤት ፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍ/ቤት ፣ እነ/ሳ/ም/ወ/ፍ/ቤት አግልግሎት የሚውሉ በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የተለያዩ ኤሌክትሮኒስ ዕቃዎች፣ ሎት 4 የተለያዩ የህትመት ስራዎች ሎት 5 ብትን ጨርቅ እና የሠራተኞች የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 6 የህንጻ መሳሪያዎች፣ በሎት 7 አሸዋና ድንጋይ፣ ሎት 8 እንጨት አቅርቦት፣ ሎት 9 መስተንግዶ፣ ሎት 10 አናጺ ባለሙያ እና በሎት 11 ፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
የግዥ መጠን 200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 20.00 /ሃያ ብር/ በመክፈል ከሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፍ/ቤት፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍ/ቤት፣ እነ/ሳ/ም/ወ/ፍ/ቤት፣ ከሁሉም ወረዳዎች ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር አንድ በመቶ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ( ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመቤታችን ዋ/ገ/ያዥ ደረሰኝ በማስቆረጥ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ16 ቀናት እስከ 3፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡05 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት የድርጅቱን ክብ ማህተም በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በ4ቱም ወረዳ ፍ/ቤት ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 00 59፣ 058 664 01 78 እና 058 666 01 38 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈጸም ከተገለጸለት ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ከአሸነፈበት የእቃ ወይም የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ ሃ በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አሸናፊው ተጫራች ጥራት ያለው ዕቃ በተቀመጠው ሳምፕል መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የነጠላ ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋ፣ ማስቀመጥና የድርጅቱ ማህተም፣ ስምና፣ ፊርማ፣ አድራሻና፣ ስ.ቁ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያመጣ (የሞላ) ነው፡፡
ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ፖራፍ ማድረግ አለበት፡፡
አሸናፊው የሚለየው እንደ አስፈላጊነቱ በጠቅላላ ድምር ውጤት በሎት በመሆኑ የተጠየቁትን እቃዎች ዝርዝር ሁሉንም አካተው መሙላት አለባቸው፡፡
የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ የሥራ ቀንና ስዓት ይከፈታል፡፡
አሸናፊ ተጫራች የአሸነፋባቸውን ሁሉንም አይነት እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት /የሚሞሉት/ ዋጋ ማንኛወንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
በተጨማሪም በግዥ አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው የጨረታ በጨረታ መክፈቻ ጊዜና ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
አሸናፊው ተጫራች ዉል የያዘባቸዉን ዕቃዎች ጠቅሎ በ3ቱም ወረዳ ፍ/ቤት ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፍርድ ቤት ቁ 1