በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አማካይነት ለሴክተር መ/ቤቶች የ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ሎት-1 የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃ፣ ሎት 3 ቋሚ አላቂ፣ ሎት 4 የሚዘጋጅ ፈርኒቸር፣ ሎት 5 የተዘጋጀ ፈርኒቸር እና ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየ አንዳንዱ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 18 ከ25/02/2017 ዓ/ም እስከ09/03/2017 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን በተከታታይ ቀናት እስከ 10/03/2017 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 10/03/2017 ዓ/ም በ16ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 18 በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነዉ፡፡
ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በፍጥነት ዕቃውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ማንኛውም ተወዳዳሪ የጽ/መሳሪያ፣ የፅዳት እቃ፣ ቋሚ አላቂ፣ የሚዘጋጅ ፈርኒቸር፣ የተዘጋጀ ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃ ጽ/ቤቱ ያቀረበውን ስፔስፊኬሽን በትክክል በማየት መወዳደር ይኖርበታል፡፡
ጨረታዉ የሚከፈተዉ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የካላንደር በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ በሥራ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 07 95 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም፡፡
የቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት