የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከባህልና ቱሪዝም ጋር በትዕዛዝ ለፕሮጀክት ሥራ የሚሆን ብረታ ብረቶች፣ ለኤሌክትሪክሲቲ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮንስትራክሽን፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ሰርቫይንግ ድራፍቲንግ ትህምርት ክፍሎች ማሰልጠኛ ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አውዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ማንኛዉም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸዉ መሳተፍ መጫረት የምትችሉ መሆኑን አየገለፅን፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
የግዥዉ መጠን 100,000.00 /አንድ መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስጥር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
የጨረታው ዉድድሩ ነጠላ ድምር ዋጋ ሆኖ አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት እቃዎችን በራሱ ወጭ በማጓጓዝ በባለሙያተኞች እየተረጋገጠ ዕቃዎችን ገቢ ይደረጋል፡፡
የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የለበትም፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት 70,000.00 /ሰባ ሽህ ብር/ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮሌጁ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ወይም ገጽ ላይ ፊርማ እና የድርጅቶች ማህተም በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በአየር ላይ የዋለበት ቀን ከ25/02/2017 ዓ.ም እስከ 18/03/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሥዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 እንዲሁም በ19/03/2017 ዓ.ም እሰከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል በ19/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት ወይም ቁጥር 058 111 83 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ለተከታታይ 16 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ የሥራ ቡድን ቢሮ በመምጣት 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፍል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ