ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
147

የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ሴ/መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ ሎት 4 የጽዳት እቃ፣ ሎት 5 ህትመት፣ ሎት 6 ፈርኒቸር እና ሎት 7 የፋብሪካ እቃዎችን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና 2016 ዓ.ም የስራ ግብር ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ያጠናቀቀ መሆን ይኖርበታል፡፡ (የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ጨረታ ማስከበሪያ ብር አንድ በመቶ የጨረታ ሳጥኑን ከመከፈቱ ቀድሞ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

ተጫራቾች ያሸነፉትን የእቃ ዋጋ አስር በመቶ ወድያዉኑ በማስያዝ ዉል በመዉሰድ የተጠየቀዉን እቃ ጥራት ጠብቆ ሊያቀርብ ይገባል፡፡

ያሸነፉበትን እቃ ለማቅረብ ዉል የማይወሰድ ወይም ዉል ከወሰደ በኋላ እቃዉን የማያቀርብ ተጫራች ቢያጋጥም መ/ቤቱ ለዉል ማስከበሪያ የያዘዉን ገንዘብ መዉረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ 1 ዓመት ለሚደረስ ጊዜ በጨረታ እንዳይሳተፍ የማገድ ስልጣኑን ለመጠቀም ይገደዳል፡፡

ማንኛዉም ተጫራች የማወዳደሪያ ዋጋ ሲሞላ አንድ ኦርጅናል በአንድ ፓስታ ወይም አንድ ኮፒ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ አሽጎ ማስገባት ይቻላል፡፡

ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

ማንኛዉም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን የማይመለስ 1 ኮፒ የግብር ከፋይ ምዝገባ 1 ኮፒ፣ ቫት (ቲኦቲ) የምስክር ወረቀት የማይመለስ 1 ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡

ማንኛዉም ተጫራች ለሚያቀርበዉ እቃ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ሊኖረዉ ይገባል፡፡

ማንኛዉም ተጫራች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ታሰቦ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ መ/ሰ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን /ቢሮ ቁጥር 210 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡

ጨረታዉን በዚሁ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሲሆን ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ስዓት ይከፈታል፡፡

የሚገዛው እቃ ጽ/ቤታችን ባዘጋጀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ጥራቱን ጠብቆና ባዘጋጀነው ናሙና  መሰረት መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

ጨረታው በሎት የሚካሄድ መሆኑ ታውቆ ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በሚሞላበት ጊዜ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል፡፡

በጨረታዉ ያሸነፈዉ ግለሰብ የሚያቀረበዉን እቃ መ/ሰ/ከ/አስ/ ግቢ ድረስ የሚያመጣዉ በራሱ ወጭ መሆኑ ይታወቅ፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት የሚፈልጉ በስልክ ቁጥር 09 29 46 21 01 ወይም 09 14 45 28 92 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here