ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
197

የቢቡኝ ወረዳ ግ/ፅ/ቤት በብ/የሚ/የግ/ግክ/ቡድን በ2017 በጀት አመት ለፅ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የደን ዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የብቃት ማረጋገጫ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ  (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

የግዥ መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የመስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የደን ዘር ማለትም፡- ጌሾ 120 ኪ/ግ፣ ግራቪሊያ 60 ኪ/ግ፣ የፈረንጅ ፅድ 40 ኪ/ግ፣ ወይራ 40 ኪ/ግ፣ የፈረንጅ ግራር 50 ኪ/ግ፣ የሃበሻ ፅድ 40 ኪ/ግ እና ሞሪንጋ 30 ኪ/ግ ሁኖ እቃውን ሲያቀርብ ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ፣ የአሰሪው መ/ቤት እና የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ፣ ማህተም በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት 30.00 /ሰላሳ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ከቢ/ወ/ገ/ኢ/ል/ፅ/ቤትደ/ሂ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡

ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢ/ወ/ግ/ፅ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ 25/02/2017 ዓ.ም እስከ 13/03/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡

ጨረታዉን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግብ/ፅ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን በቢሮ ቁጥር 06 በ14/03/2017 ዓ.ም በ 3፡00 ይከፈታል፡፡

አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ሃ በመቶ የመጨመርም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

መ/ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን ብሄራዊብ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡

አሸናፊው ድርጅት የተጠየቁ ግብዓቶችን በሙሉ ቢ/ወረዳ ግብርና ፑል ንብረት ክፍል በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይደረጋል፡፡

ሰለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 06 04 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና /ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here