ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
122

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ለመንገድ መብራት ቅያር ለመቆጣጠሪያነት የሚያገለግሉ ኤሌክትሪክ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው፡፡

በስሙ የታተመ ማህተምና ደረሰኝ ያላቸዉ፡፡

የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 100,000.00 /አንድ መቶ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ 02/03/2017 ዓም እስከ 17/03/2017 እስከ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 1,000.00 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በቀጣዩ ቀን በ18/03/2017 ዓ.ም ቀን በ4፡00 ይከፈታል ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታዉን ለመክፈት እንገደዳለን፡፡

አሸናፊዉ የሚለየዉ በእያንዳንዱ እቃ ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማጓጓዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብረት አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 18 78   መደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here