ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በወረዳው ውስጥ ላሉት መኪኖች የመኪና መለዋወጫና የመኪና ጎማ ከነ ካመዳሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋ፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማለትም፡-

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከሁ/እ/እ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ከረዳት ገ/ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ለመኪና መለዋወጫ 50,000 /አምሣ ሺህ ብር/ ለመኪና ጉማ 24,000.00 /ሀያ አራት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገንዘብ የሚያስይዙ ገንዘቡ በሁ/እ/እ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ እና መሂ 1 ከሰነዱ ጋር መያያዝ አለበት፡፡

አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተገለፀበት ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት የዕቃ /አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የተሸከርካሪ ኩንትራት ጥገና ከሆነ ሶስት በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ፕሮፎርማንስ ቦንድ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይን በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank grante/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሁ/እ/እ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስ ከ 16 ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ መወዳዳሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት ለመ/ቤቱ እና ለተጫራቾቹ ለደህንነት እንጂ እንደመወዳሪያ መስፈርት አይሆንም፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ  በወጣበት 16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን መክፈት መብት አለው፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡

ውድድሩ በሎት ስለሆነ በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሱትን ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቹህ፡፡

አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጭ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ንብረት ክፍል ገቢ ሊያደርግ የሚችል፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት   ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 19 35 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here