ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ፖ/ቴ/ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም የበጀት ዓመት የኮሌጁ አገልግሎት የሚውል እቃ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሎት ግጨፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡- ሎት 1 የኮንስትራክሽን ተዛማጅ እቃዎች ሎት፣ 2 ኤሌክትሮኒክስ ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3 የፅህፈት ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 4 የግብርና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 5 አውቶ ሞቲቭ   እና ሎት 6 የደንብ ልብስ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡

የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

በዘመኑ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ከፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰቆጣ በፀደይ ባንክ ገቢ አድርጎ አድቫይስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የጨረታ አሸናፊዎች በ10 ቀን ጊዜ ውስጥ ቀርበው ሙል በመፍፅም የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ባያሲይዙ የጨረታ አሸናፊነታቸውን ተሰርዞ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘቡ የማይመለስ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም እቃን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትናና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች ሂሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ (ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳር ዞን የሰቆጣ ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በግዥ ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ከ 02/03/2017 ዓ/ም እስከ 22/03/2017 ዓ/ም ድረስ አስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርበታል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በሠቆጣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር6 በ23/03/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ላይ ይከፈታል፡፡

መስሪያ ቤቱ ወይም ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስክ ቁጥር 09 38 91 67 38 /09 88 60 01 19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ በዚህ ጨረታ ላይ አሸናፊ ሆነው ቢገኙ ንብረቱ ሠ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ድረስ በመምጣት በባለሞያ ንብረቱ ተረጋግጦ የሚያስረከቡ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ፖስታውን በምንከፍትበት ስዓት ተጫራቾች ነጋዴዎች ህጋዊ ወኪሎች በማይቀርቡበት ፖስታውን ማስከፈት እንችላለን ሰነዱን ሲሞሉ ቫት ጨምረው ይሙሉ፡፡

የሰቆጣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here