የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለሆስፒታሉ ግልጋሎት የሚውሉ 1. የተለያዩ መድኃኒቶች ፣ 2. የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ 3. የተለያዩ የላብራቶሪ ሬጀንቶች፣ 4. የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ 5. የተለያዩ የጥገና እቃዎች፣ 6. የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣ 7. የተለያዩ ህትመቶች፣ 8. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ 9. የተለያዩ የተሸከርካሪና የጀኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች፣ 10. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 11. የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣ 12. የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች ጥገና ስራ፣ 13. የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎች 14. የደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፤ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ ከተራ ቁጥር 1እስከ ተራ ቁጥር 3 የሚጫረቱ አሸናፊው የሚለየው በየአሸነፉበት ሲሆን ከተራ ቁጥር 4 እስከ ተራ ቁጥር 14 አሸናፊው የሚለየው በሎት ድምር ነው፡፡
ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
የተጫራቾች ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢመሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርትፍኬት ከሌሎች መረጃዎች ጋር አብሮ መያያዝ አለበት፡፡ መድሃኒት፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና ሬጀንቶች ከ200,000 ብር በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው የሚለው አያካትታቸውም፡፡
የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ድምር 10 ሺህ ብር በላይ ከሆነ 2በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ቫት 7.5በመቶ ይቀንሳል፡፡
ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ፣ 1በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 259 ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራችው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም ፡፡
የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከ02/03/2017 ዓ.ም እስከ 23/3/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ21 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 ለተዘረዘሩት በ23/03/2017 ዓ.ም እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ23/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ከተራ ቁጥር 4 እስከ 14 የተዘረዘሩት ደግሞ በ24/03/2017 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጧቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስራ ሂደቱ ስልክ 0333310172 እና 0333310252 ደወሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው መጠን ማቅረብ አለበት፡፡
ለመድሃኒቶች የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ የላብራቶሪ ሬጀንቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች ጥገና፣ ህትመቶች፣ የተሸከርካሪ እና የጀኔሬተር መለዋወጫዎች፣ የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ የሚያቀርብ ሲሆን ሌሎች ከዚህ ውጭ የተዘረዘሩት ደግሞ አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ወራት ድረስ ሆስፒታሉ አቅርብ ብሎ ሲያዘው በታዘዘው ቀን ውስጥ ግብአቱን ( እቃውን ) ወይም የጥገና ስራውን ማቅረብ ወይም መስራት አለበት፡፡
መድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎች እንዲሁም የላቦራቶሪ ሬጀንቶች እንዲቀርቡ የሚታዘዘው ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት የሌለ መሆኑ ሲረጋገጥና ሆስፒታሉ አስፈልጎት ለአሸናፊዎች የግብአት አቅርቦት ጥያቄ ሲያቀርብ ነው፡፡
የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል