ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ስልጠና ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 የፕሪተር ቀለም፣ ሎት 5 የቢሮ ጥገና እቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ጎማ፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 8 የተዘጋጅ አልባሳት እና ሎት 9 ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ ሰነዱ መሠረት መወዳደር ይችላሉ፡፡

አግባብነት ያላቸው ህጋዊና በዘርፉ የተሰማሩ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 01 በመክፈል የጨረታ ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ፡፡

ግዥው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ከፖስታው ላይ በመጻፍ ቢሮ ቁጥር G001 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ስትወዳሩ የምታቀርቡትና ዋጋ የምትሞሉት በኦርጅናል ዕቃ ብቻ መሆኑን ማወቅ ይጠበቅባችኋል፡፡ቴክኒካል የሚያስፈልጋቸው ኤሌክትሮኒክስ እና የመኪና ጎማ ግዥቴክኒካልና ፋይናሸያል በሚል ሁለት ፖስታዎች ማስገባት አለባችሁ፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 2 12000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 9000 /ዘጠኝ ሺህ ብር/ ለሎት 4 ብር 15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 5 ብር 4500 /አራት ሺህ አምስት መቶ/ ለሎት 6 ብር 30000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 7 ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ ለሎት 8 ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት 9 ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው የገቢ ደረሰኝ በማሰቆረጥ ማስረጃዉን ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ጨረታዉ ከተከፈተ በኃላ ጨረታ ሰነድ ላይ የተሞላን ዋጋ ማሻሻል ፣ መለወጥ ወይም ጨረታዉን ሰርዣለሁ የሚሉት ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ማለትም 17//03/2017 ዓ/ም ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ባህርዳር ዳር ከተማ በሚገኘው  ስራና ስልጠና ቢሮ ቁጥር G001 ውስጥ ይከፈታል፡፡ አስራ ስድስተኛው ቀን  ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም  የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ውድድሩ በሎት ድምር ሲሆን ሎት 6 የመኪና ጎማ ግን ውድድር በተናጠል መሆኑን አውቃችሁ መሙላት ይኖርባችኋል፡፡

ቢሮዉ ጨረታዉን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ /መረጃ/ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 53 97 መጠቀም ይችላሉ፡፡

የአብክመ ስራና  ስራና ስልጠና ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here