ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

የአብክመ ክ/ም/ቤት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት በ2017 በጀት ዓመት ለአብክመ ክ/ምክር ቤት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ሎት 01. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 02. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 03 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 04. የመኪና ጎማና የቅባት እቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

በዘርፉ ህጋዊ /ወቅታዊ/ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለአብክመ ም/ቤት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት  ቢሮ ቁጥር 43 ለሥራው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡

የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ  በየሎቱ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት አብክመ ም/ቤት ጽ/ቤት/ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 48 መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በየሎቱ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና  ወይም  በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ለጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመክፈል  የደረሰኙን ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10.የጨረታው አሸናፊ የሚለየዉ በሎት /በጥቅል / ድምር ዋጋ ስለሆነ ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸዉ፡፡

ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ /በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ /ማስያዝ/ ይኖርባቸዋል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 0582262151 ይደውሉ ወይም ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 40 በአካል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡

የአብክመ ም/ቤት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here