ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
104

የአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የተለያዩ የዉሃ መሳቢያ ፓምፖችን ግዥ የፈፀመ በመሆኑና እነዚህን ፓምፖች በክልሉ ለሚገኙ 10 /አስር/ ዞኖች ለማሰራጨት ስለፈለገ ከባህር ዳር ወደ ዞኖች ከተማ የሚያጓጉዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዉል ይዞ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

የሚጓጓዙትን የዉሃ መሳቢያ ፓምፕ ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ02/03/2017 ዓ.ም እስከ 16/03/2017 ዓ.ም ድረስ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 37 ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 10,000.00 ( አስር ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ዉድድሩ በነጠላ ዋጋ መሆኑን አዉቀዉ የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሸገዉ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 37 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ02/03/2017 ዓ.ም እስከ 16/03/2016 ዓ.ም 3፡30  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ጠቅላላ ብዛት እና ለእያንዳንዱ ዞን የተደለደለዉን ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጨረታዉ ከተከፈተ እና አሸናፊዉ ከተለየ በኋላ ፓምፖች በአስቸኳይ ለመስኖ ልማት አገልግሎት መድረስ ስላለባቸው ተጫራቾች በቂ የሆነ የጭነት ተሸከርካሪ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 17/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ4፡00  ይከፈታል፡፡

ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 37 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 08 17 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

አድራሻ ባ/ዳር ቀበሌ 08 ባ/ዳር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 37

የአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here