ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
108

የደብረ ማርቆስ/ማ/ከ/አስ/ተ/ጓ/ክ/ከ ለሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ በሎት ጠቅላላ ድምር ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ኮምፒውተር እና ፕሪንተር፣ ሎት 3. የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡  የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።

የግዥው መጠን ቫት የሚገባ ከሆነ ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1—2 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

የሚገዙትን ዕቃ አይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

የኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና ተ/ጓ/ክ/ከ ግዥና ፋ/የስ/ሂደት ቡድን ቢሮ ድረስ በመምጣት መጠገን የሚችል መሆን አለበት፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱና ማህትም ማድረግ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ሴፔስፍኬሽን ለቀረበላቸው በሴፔስፍኬሽን መሰረት ላልቀረበላቸው ዕቃ በባለሙያ ተረጋግጦ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል፡፡

ተጫራቾች በሚሞሉት ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ተ/ጓ/ክ/ከ ግዥና ፋ/የስ/ሂደት ቡድን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም  በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /አጠቃላይ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ/ 1 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ሞልቶ በታሸገ ፖስታ ተ/ጓ/ክ/ከ ግዥና ፋ/የስ/ሂደት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ በአየር ላይ ይውላል፡፡

የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተ/ጓ/ክ/ከ ግዥና ፋ/የስ/ሂደት ቡድን ቢሮ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

አሸናፊው ድርጅት ተ/ጓ/ክ/ከ ግዥና ፋ/የስ/ሂደት ቡድን ቢሮ ን/ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ይዞ በመምጣት ማስረከብ አለበት፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልክ 058 178 0446 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የደብረ ማርቆስ/ከ/አስ/ተ/ጓ/ክ/ከ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here