ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአዲስ አለም ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ  3 ዓይነት ማለትም ሎት 1 የተለያዩ የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ እና ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ ስለመሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከግ/ፋ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ማግኝት ይችላሉ፡፡

በሎት የወጡ  3ቱም አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኃላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በታሸገ ፖስታ በአዲስ አለም ሆስፒታል ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፅበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ያስይዛል፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 34 ደውለው ማግኝት ይችላሉ፡፡

የአዲስ አለም ሆስፒታል

ባ/ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here