ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
153

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለሰ/ጎ/ዞ/ጤና መምሪያ በዳባት ወረዳ ወቅን ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል ባለ5 ቀዳዳ ሽንት ቤት እና 1 ሻወር ቤት ያለው ግንባታ ሙሉ ማቴሪያል በተቋራጩ ሆኖ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ  ማስገንባት  ይፈልጋል፡፡  ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባው፡-

በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው፡፡

ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ  ብር/ እና በላይ ከሆነ   የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

በሁለት አመት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የህንጻ ተቋራጭ ፈቃድ ያላቸው፡፡

ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ/ በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም በመ/ቤቱ ዋና ገ/ያዥ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ እና ሲፒኦ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ለግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ሙሉ  የግንባታውን የሥራ ዝርዝር  ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን  በማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰ/ጎ/ዞ/ገንዘብ መምሪያ ዋ/ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን አሰተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥና  ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋና እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ሰ/ጎ/ዞ/ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን  ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን  ከ 02/03/2017 እስከ 22/03/2017 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1  በቀን 23/03/2017 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ  በ4፡30 የከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ  ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡

የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ  ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

መስሪያ ቤቱ  ይህንን ግንባታ የተሻለ  አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጨረታ መክፈቻ ቀን ብሔራዊ በዓል ወይም  ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡

በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 417 00 30  /40 06/ 09 18 25 26 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here