ቁጥር 02/2017
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሎት 1 የአጠቃላይ የህንፃዎች የአስተዳድር፣ የራዲዮ እና ቴሌቪዥን ህንፃዎች የዉጭ ቀለም ቅብ እና ጥገና ሥራ ለማሰራት የህንጻ እና የጠቅላላ ተቋራጮችን ከደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ ብቻ የሚሳተፉበት፣ ሎት 2 የስልጠናና ምርምር የኤፍኤም ራዲዮ ስቱዲዮ ኢንቴረር ሥራና አጠቃላይ ጥገና ሥራ ለማሰራት የህንፃ እና የጠቅላላ ተቋራጮችን እንዲሁም የማጠቃለያ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ ከደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ ብቻ የሚሳተፉበት እና ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ዘዴ በጋዜጣ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ለግንባታ ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት 1 እና 2 ለተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ ቀን እንዲሁም ሎት 3 ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡ ሰነዱን በጥንቃቄ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በመሙላት የፋይናስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የግንባታ ሰነዶችን እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፣ የጽህፈት መሳሪያ እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማሰገባት አለባቸዉ፡፡ በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸዉ መ/ቤት የቅርብ ጊዜ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ለሎት 1 እና 2 በ22ኛው ቀን ሎት 3 በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው እና 16ኛዉ ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የህንፃ የቀለም ቅብ፣ የጥገና እና የኢንተርኔት ሥራዉ፣ የጽህፈት መሳሪያ ዓይነት፣ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 70 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር